መግለጫዎች

 እንዶድ

ሌሎች የሃገር ውስጥ ስሞች፡- አንዶተ፣ አንዶድ፣ ሃንዱዲ (ኦ)፣ አዛብ፣ሀሰረ(ግ)፣ መካን እንዶድ (አ) ሰበት(ት)፣ ሸብጢ (ትግ) ፣ሲቢል(ሳ)፣ ጎኖፋይ (በ)፣ ሾርሹ(ሻ) ስነ ዕፃዊ ስም፡- ፋይቶላካ ዶዴካንድራ (Phytolacca dodecandra) ቤተ ዘመድ፡- ፋይቶላኬሲ (phytolaccaceae)

ስርጭት

እንዶድ በ1,500 ሜ.ከበ.ወ.በ. ከፍታ ላይ ዝቅተኛ የደን ሽፋን ባላቸው ወንዞች ዳርቻ ይበቅላል፡፡ እንዲሁም በዝርሂ ዳኩሊ ተራሮችና በትስኪ ፏፏቴ አጠገብ በደኖች ውስጥ በተጎዱ አካባቢዎች ይገኛል፡፡ እንዶድ ከአፋር ክልል በስተቀር በመላው ኢትዮጵያ ይበቅላል፡፡

የዕፁ መግለጫ

እንዶድ ብዙ ቅርንጫፎች ያሉ ግንዱ እስከ ዘጠኝ ሜትር የሚረዝም ከእንጨትማ መሰረት ተነስቶ የሚያድግ የቁጥቋጦ ዝርያ ነው፡፡ ቅጠሎቹ የተዘበራረቁ ሆነው የዕንቁላል ቅርፅ ይይዛሉ፡፡ አበባዎቹ መዓዛማ መልካበባ አላቸው፡፡

ምንጭ፡- ዶ/ር ፈቃዱ ፉላስ በአሜሪካን አገር “የኢትዮጵያ ባህል መድኃኒት በሳይንሳዊ አቀራረብ -
የመድኃኒት ዕፅዋት” ብለው ካሳተሙት መፅሐፍ - በደራሲው ፈቃድ የተወሰደ