የአትክልት ቦታዎች

ለመድሀኒት ለመዓዛና ለጣዕም የሚጠቅሙ አያሌ አገር በቀልና መጤ ዕፅዋት አሉ :: እነዚህን ለማብቀለና በስፋት ለማምረት በመጀመርያ ደረጃ ችግኞችንና ዘር ማዘጋጀት ያስፈልጋል:: ይኸ ለማዘጋጀት ከአዲስ አበባ 27ኪሎ ሜትር ርቀት ሰበታን አለፍ ብሎ አቦ ቤ/ክ አጠገብ 1 ሄክታር የሚሆን የተክል ቦታ አለን:: በዚህ የተክል ቦታ ላይ በርከተ ያሉ ዕፅዋት እንከባከባለን:: ከነዚህም መሀል ጠጀሣር፣ ሲትሮኔላ፣ሬት፣እንስላል፣ የቻይና ጭቁኝ፣ ላቨነደር ወ.ዘ.ተ:: የተክል ቦታው የሚገኝበትን ቦታ ጠቋሚ ከዚህ በታች ይኖራል:: ከዚህ ገፅ ጀርባ የሚተታየወው ፎቶግራፍ ሰበታ የሚገኘው የተክል ቦታችን ነው፡፡