እንኳን ወደ አሪቲ ኸርባል ድረ ገፅ መጡ

አሪቲ እኤእ በ1999 የተቋቋመ በማምረትና በንግድ ሥራ ላይ የተመሰማራ አነስ ያለ ድርጅት ነው:: ዋና አላማችን ለውብትና ለጤንነት ተስማሚ ከሆኑ አገር በቀልና መጤ ዕፅዋት መአዛማ ውጤቶችን በልዩ ልዩ ዘዴዎች ማውጣትና ለተጠቃሚዎች ማቅረብ ነው:: አሪቲ የሚለውን የንግድ ስም የመረጥነው ይህ ስም የሚወክለው ዕፅ መዓዛ ያለው በመሆኑ ለድርጅታችን መጠሪያ ተስማሚ ነው ብለን ስላመንን ነው:: ከዕፅዋት በፈላ ውሀ አማካኝነት የሚወጣውን ተን በማቀዝቀዝና ከውሀው በመለየት መዓዛማ ዘይት ማውጣት ይቻላል:: በዚህ ዘዴ ከባህር ዛፍ፣ ሎሚ ሳር፣ ጦስኝ፣ ሮዛ ማሪኖ፣ ላቨንደር፣ ወዘተ... ና ከሌሎች ተን ዘይት ማውጣት ይቻላል:: በተን ዘይት ልዩ ልዩ ዘዴዎችን በመጠቀም በተለይ ለፀጉርና ለቆዳ እንክብካቤ፤ ሰውነትን ለማሸት፤ ፊትን ለማበስ፤ ገላን ለመታጠን፤ አፍን ለመጉመጥመጥ ወ.ዘ.ተ. መጠቀም ይቻላል:: እነዚህን ውጤቶች ደንበኞቻችን ከድርጅታችን በማዘዝ ወይም መደብራችን በመምጣት ሊያዩና ሊገዙ ይችላሉ:: ሌላው የዕፅ መጠቀሚያ ዘዴ በሻይ መልክ መውሰድ ነው:: አንድ ሾርባ ማንኪያ ደቀቅ ያለ ዕፅ ወይም ድብልቅ ዕፅ የፈላ ውሀ ውስጥ 5 ደቂቃ ያህል እንዲቆይ ቢደረግ ዕጹ ውስጥ ያሉት ጠቃሚ ውሁዶችና ንጥረ ነገሮች ተመዝምዘው ይወጣሉ:: ይህን ሻይ መጠጣት ጠቃሚነቱ ግልፅ ነው:: መዓዛማ ዕፅዋቶች ልዮ ማጣፈጫ እይፈልጉም:: ካለስኳር ሊጠጡ ይችላሉ:: ድርጅታችን ባለፈው 15 ዓመት ባመረተው ምጥን የዕፅዋት ሻይ ብዙ ሺህ ደንበኞቻችን ረክተውበታል:: የዘውትር የዕለት ተዕለት ሻያቸውም አድርገውታል:: የዚህ ድረገጽ ዋና አላማ ደንበኞቻችንን ስለ ዕፅዋት ጥቅም በተለይ ለውበትና ለጤንነት እንዴት እንደሚውሉ ማስረዳት ነው::

 • Hair Tonic
 • Natural Massage Oil
 • Room Freshener,
  Lemon Scented
 • Black Cumin Oil
 • Lemongrass Oil
 • Eucalyptus-Mint Blend
 • Frankincense
 • Senna Laxative Tea
 • Stevia, Sweet Leaf Tea
 • Balanced Herbal Tea
 • Balanced Herbal Tea
 • Lupinus albus
  Gebto (Amh).
 • Boswelia papyrifera
  Etan (Amh)
 • Taverniera abyssinica
  Dengetegna (Amh)

አድሻችን

AritiShopLocator